Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሎጥ ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፣ የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ እንደ እግዚአብሔር ገነት፣ በዞዓር አቅጣጫ እንዳለው እንደ ግብጽ ምድር ውሃማ ቦታ ሆኖ አገኘው። እንዲህም የነበረው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 13:10
26 Cross References  

ምድረ በዳ​ውን፥ የኢ​ያ​ሪ​ኮን ዙሪያ፥ እስከ ሴይር ዙሪያ ያለ​ው​ንም የፊ​ን​ቆ​ንን ከተማ አሳ​የው፤


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ደስ አሰ​ኝ​ሻ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ሽ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ሽ​ንም እንደ ዔድን፥ በረ​ሃ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ደስ​ታና ተድላ እም​ነ​ትና የዝ​ማሬ ድምፅ በው​ስጧ ይገ​ኝ​ባ​ታል።


የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤


እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ከሰ​ዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገ​ሞራ ንጉሥ ከበ​ርሳ፥ ከአ​ዳማ ንጉሥ ከሰ​ና​አር፥ ከሲ​ባዮ ንጉሥ ከሲ​ም​ቦር፤ ሴጎር ከተ​ባ​ለች ከባላ ንጉ​ሥም ጋር ጦር​ነት አደ​ረጉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት በዔ​ድን ነበ​ርህ፤ የከ​በረ ዕን​ቍስ ሁሉ፥ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ አል​ማዝ፥ ቢረሌ፥ መረ​ግድ፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፥ ሰን​ፔር፥ በሉር፥ የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ፥ ወር​ቅም ልብ​ስህ ነበረ፤ የከ​በ​ሮ​ህና የእ​ን​ቢ​ል​ታህ ሥራ በአ​ንተ ዘንድ ነበረ፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በ​ትም ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ነበር።


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በተ​ር​ታን መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አስ​ፈ​ሰ​ሰው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት የነ​በሩ ዝግ​ባ​ዎች አይ​ተ​ካ​ከ​ሉ​ትም፥ ጥዶ​ችም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን፥ አስታ የሚ​ባ​ለ​ውም ዛፍ ጫፎ​ቹን አይ​መ​ሳ​ሰ​ሉ​ትም ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት ዛፍ ሁሉ በው​በቱ አይ​መ​ስ​ለ​ውም ነበር።


ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና።


ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።


አራ​ንም ሎጥን ወለደ።


እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።”


ሎጥም ለራሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥ​ራቅ ተጓዘ፤ አን​ዱም ከሌ​ላው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ።


በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”


እነሆ፥ ወንዙ ቢጐ​ርፍ አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈ​ስስ እርሱ ይተ​ማ​መ​ናል።


ታላ​ቂ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በስተ ግራሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰማ​ርያ ናት፤ ታና​ሽ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰዶም ናት።


እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።


በጫ​ፎቹ ብዛት ውብ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት በዔ​ድን የነ​በሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑ​በት።


የም​ሥ​ራ​ቁም ድን​በር በሐ​ው​ራን በደ​ማ​ስ​ቆና በገ​ለ​ዓድ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖስ ይሆ​ናል። ከሰ​ሜኑ ድን​በር ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የም​ሥ​ራቁ ድን​በር ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements