Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ብ​ራም ሚስት በሦራ ምክ​ን​ያት ፈር​ዖ​ን​ንና የቤ​ቱን ሰዎች በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት መታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና ቤተ ሰዎቹን በጽኑ ደዌ መታቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ነገር ግን በአብርሃም ሚስት በሣራይ ምክንያት እግዚአብሔር በእርሱና በባለሟሎቹ ሁሉ ላይ አሠቃቂ በሽታዎች አመጣባቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 12:17
8 Cross References  

ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ትን ገሠጸ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ብ​ር​ሃም ሚስት በሣራ ምክ​ን​ያት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ቤት ማኅ​ፀ​ኖ​ችን ሁሉ በፍ​ጹም ዘግቶ ነበ​ርና።


ዳዊ​ትም ኦር​ናን፥ “በላዩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአ​ው​ድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥ​ልኝ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከሕ​ዝቤ ይከ​ለ​ከ​ላል” አለው።


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


አብ​ር​ሃ​ምም ወደ እግ​ዚ​ዘ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ፈወ​ሳ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወለዱ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements