Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አራ​ንም ሎጥን ወለደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፥ ሐራንም ሎጥን ወለደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የአብራም፥ የናኮርና የሃራን አባት የነበረው የታራ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ ሃራን ሎጥን ወለደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራም አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 11:27
10 Cross References  

እነ​ር​ሱም የአ​ብ​ራ​ምን የወ​ን​ድም ልጅ ሎጥ​ንና ገን​ዘ​ቡን ይዘው ሄዱ። እርሱ በሰ​ዶም ይኖር ነበ​ርና።


አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የና​ኮር አባት ታራ፥ አስ​ቀ​ድ​መው በወ​ንዝ ማዶ ተቀ​መጡ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ።


አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ ለአ​ብ​ር​ሃም እን​ዲህ ተብሎ ተነ​ገረ፥ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወ​ን​ድ​ምህ ለና​ኮር ልጆ​ችን ወለ​ደች፤


አብ​ር​ሃም የተ​ባ​ለው አብ​ራም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements