Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዕዝራ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሀ​ገ​ሩም ካሉት አሕ​ዛብ ፈር​ተው ነበ​ርና መሠ​ዊ​ያ​ውን በስ​ፍ​ራው ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ በጥ​ዋ​ትና በማ​ታም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ቡ​በት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዙሪያቸው ካሉት አሕዛብ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም፣ መሠዊያውን በቀድሞው መሠረት ላይ ሠሩ፤ በመሠዊያውም ላይ ጧትና ማታ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በምድሩ ካሉት ሕዝቦች የተነሣ ፈርተው ነበርና፥ መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት በጠዋትና በማታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የተመለሱት ምርኮኞች በምድሪቱ ከሚኖሩት አሕዛብ ተቃውሞ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም እንኳ መሠዊያውን በዚያው ቀድሞ በቆመበት ቦታ መልሰው ሠሩት፤ ከዚያም በኋላ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ጠዋትና ማታ በዚያ ላይ እንደገና ማቅረብ ጀመሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በአገሩም ካሉት አሕዛብ ፈርተው ነበርና መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት፥ በጥዋትና በማታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡበት።

See the chapter Copy




ዕዝራ 3:3
11 Cross References  

የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ እጅግ ያዳ​ክሙ ነበር፤ እን​ዳ​ይ​ሠ​ሩም ከለ​ከ​ሉ​አ​ቸው፤


ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋዩ ሙሴን እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሁል​ጊዜ ጥዋ​ትና ማታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ።


‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው።


የም​ድ​ጃ​ውም ርዝ​መት ዐሥራ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነው፥ አራ​ቱም ማዕ​ዘን ትክ​ክል ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements