| ዕዝራ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በስደት በሚኖርባቸው ከተሞች ሁሉ ለቀረው ሰው ሁሉ የሀገሩ ሰዎች በብርና በወርቅ፥ በዕቃም፥ በእንስሳም ይርዱት፤ ይህም በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት ሌላ ይሁን።”See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ባሉበት ስፍራ የሚቀሩ በየትኛውም አገር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስጦታ እንዲሆን ከበጎ ፈቃድ ስጦታ በተጨማሪ ብርና ወርቅ፣ ዕቃና እንስሳ በመስጠት ይርዷቸው።’ ”See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከሁሉም ስፍራዎች የተረፈው ሁሉ መፃተኛ ሆኖ በሚኖርበት የሰፈሩ ሰዎች በብርና በወርቅ በዕቃም በእንስሳም ይርዱት፥ ይህም በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት መባ ጋር ይሁን።”See the chapter አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እነዚህ ከሞት የተረፉት ሰዎች በሚመለሱበት ጊዜ በአካባቢአቸው የሚኖሩ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ዕቃና የጭነት ከብቶች ይርዱአቸው፤ ይህም በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው ከሚሰጡት መባ ሌላ ነው።”See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በሚኖርበትም ስፍራ ሁሉ ለቀረው ሰው የአገሩ ሰዎች በብርና በወርቅ በዕቃም በእንስሳም ይርዱት፤ ይህም በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት ሌላ ይሁን።’”See the chapter |