ኤፌሶን 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እንግዲህስ ወዲህ በእግዚአብሔርና በኀይሉ ጽናት በርቱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በቀረውስ በጌታና በእርሱም ታላቅ ኀይል በርቱ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። See the chapter |
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።