Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤፌሶን 5:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ዲ​ሁም ወን​ዶች ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ራሳ​ቸው አድ​ር​ገው ይው​ደዱ፤ ሚስ​ቱ​ንም የወ​ደደ ራሱን ወደደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ባሎችም እንደዚሁ ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ ሥጋቸው መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድድ ራሱን ይወድዳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደገዛ አካላቸው አድርገው ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እንዲሁም ባሎች የገዛ ራሳቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል፤ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

See the chapter Copy




ኤፌሶን 5:28
7 Cross References  

ወን​ዶ​ችም ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ ወደ​ዳት፥ ራሱ​ንም ስለ እር​ስዋ ቤዛ አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላት ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይው​ደዱ።


አለም ‘ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤’ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን?


እን​ግ​ዲ​ያስ እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ እን​ዲሁ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን እንደ ራሳ​ችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባል​ዋን ትፍ​ራው።


“ስለ​ዚ​ህም ወንድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ሁለ​ቱም አንድ አካል ይሆ​ናሉ።”


ከቶ ሥጋ​ውን መጥ​ላት የሚ​ቻ​ለው የለም፤ ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ መገ​ባት መግቡ፤ ጠብ​ቁም።


እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements