ኤፌሶን 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በፍጹም የዋህነት ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ እየታገሣችሁ፥ ለወንድሞቻችሁም እሺ እያላችሁ፥ በፍቅር እየተጋችሁና እየተባበራችሁ፥ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በትሕትናና በየዋህነት ሁሉ፥ በትዕግሥትም እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በፍቅር እርስ በርሳችሁ እየታገሣችሁ ዘወትር በትሕትና በገርነትና በመቻቻል ኑሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ See the chapter |