Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤፌሶን 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በክርስቶስ ለማድረግ የወደደውን የአሳቡን፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር በቸርነቱ በክርስቶስ አማካይነት አስቀድሞ ባቀደው መሠረት የፈቃዱን ምሥጢር እንድናውቅ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤

See the chapter Copy




ኤፌሶን 1:9
28 Cross References  

ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤


እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን።


ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር የወ​ሰ​ናት፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የፈ​ጸ​ማት፥


ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ገለ​ጠ​ልኝ እንጂ፥ እኔ ከሰው አል​ተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትም፤ አል​ተ​ማ​ር​ሁ​ት​ምም።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።


አሕ​ዛ​ብም ይህን ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አከ​በሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትም የተ​ዘ​ጋጁ ሁሉ አመኑ።


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


“ከእኔ ጋር ለምን ትከ​ራ​ከ​ራ​ላ​ችሁ? ሁላ​ችሁ ክዳ​ች​ሁ​ኛል፤ ሁላ​ች​ሁም ዐም​ፃ​ች​ሁ​ብ​ኛል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ፤


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ሰዎች በጥ​በ​ባ​ቸው በማ​ያ​ው​ቁት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ስን​ፍና በሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ያመ​ኑ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወድ​ዶ​አ​ልና።


ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ለይቶ ያወ​ጣኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ደደ ጊዜ በጸ​ጋው ጠራኝ።


ይኸ​ውም በፍ​ጹም ጥበ​ብና ምክር ለእኛ አብ​ዝቶ ያደ​ረ​ገው ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements