ኤፌሶን 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በሚወደው ልጁ የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ይኸውም፣ በሚወድደው በርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። See the chapter |