Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ስለ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትም ኀጢ​አት የጥ​ጃ​ውን ምስል ወሰ​ድሁ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ል​ሁት፤ አደ​ቀ​ቅ​ሁ​ትም፤ እንደ ትቢ​ያም እስ​ኪ​ሆን ድረስ ፈጨ​ሁት፤ እንደ ትቢ​ያም ሆነ፤ ትቢ​ያ​ው​ንም ከተ​ራ​ራው በሚ​ወ​ርድ ወንዝ ጨመ​ር​ሁት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ደግሞም ያን የኀጢአት ሥራችሁን፣ ያበጃችሁትን ጥጃ ወስጄ በእሳት አቃጠልሁት፤ ከዚያም ሰባብሬ እንደ ትቢያ ዱቄት እስኪሆን ድረስ ፈጭቼ ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንሁት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሠራችሁትንም ጥጃ ምስል፥ ኃጢአት ያደረጋችሁበትንም ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፥ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ያንንም በጥጃ አምሳል አቅልጣችሁ የሠራችሁትን በኃጢአት የተሞላ አጸያፊ ምስል አንሥቼ እሳት ውስጥ ጣልኩት፤ እርሱንም ሰባብሬ እንደ ትቢያ አደቀቅሁት፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርደው ውሃ ውስጥ ጨመርኩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።

See the chapter Copy




ዘዳግም 9:21
9 Cross References  

የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።


በዚ​ያም ቀን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እጆ​ቻ​ቸው የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይጥ​ላሉ።


ኤፍ​ሬም መሠ​ዊ​ያን አብ​ዝ​ቶ​አ​ልና የወ​ደ​ደው መሠ​ዊያ ለኀ​ጢ​አት ሆነ​በት።


በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ሊያ​ጠ​ፋው እጅግ ተቈ​ጣው፤ ስለ አሮ​ንም ደግሞ በዚ​ያን ጊዜ ጸለ​ይሁ።


የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው።


መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሰ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ችም አደ​ቀቀ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የኮ​ረ​ብ​ታ​ዎ​ችን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​አ​ጠፋ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements