Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ፤ ስለ ሰጠ​ህም ስለ መል​ካ​ሚቱ ምድር አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ እንዲህ ያለች መልካም ምድር ስለ ሰጠህ አምላክህን እግዚአብሔርን ባርከው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር ጌታን አምላክህን ትባርካለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በልተህ ትጠግባለህ፤ ይህችን ለም ምድር የሰጠህን እግዚአብሔር አምላክህንም ታመሰግናለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር አምላክህን እግዚአብሔርን ትባርካለህ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 8:10
14 Cross References  

ብር​ሃ​ንን እንደ ልብስ ተጐ​ና​ጸ​ፍህ፤ ሰማ​ይ​ንም እንደ መጋ​ረጃ ዘረ​ጋህ፤


አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል።


እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


ሕዝቡም በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።


ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።


ደግ​ሞም ጌታ​ችን የባ​ረ​ከ​ውን እን​ጀራ ከበ​ሉ​በት ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ከጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ሌሎች ታን​ኳ​ዎች መጥ​ተው ነበር።


ሳይ​ጐ​ድ​ልህ እን​ጀ​ራን ወደ​ም​ት​በ​ላ​ባት፥ አን​ዳ​ችም ወደ​ማ​ታ​ጣ​ባት ምድር፥ ድን​ጋ​ይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተ​ራ​ራ​ዋም መዳብ ወደ​ሚ​ማ​ስ​ባት ምድር ያገ​ባ​ሃል።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ካገ​ባ​ኋ​ቸው በኋላ፥ ከበ​ሉም፥ ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ይስ​ታሉ፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ወደ ማም​ለክ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እኔ​ንም ያስ​ቈ​ጡ​ኛል፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ።


አሁን የወ​ይ​ኔን ቦታ በተ​መ​ለ​ከተ የወ​ዳ​ጄን መዝ​ሙር ለወ​ዳጄ እዘ​ም​ራ​ለሁ። ለወ​ዳጄ በፍ​ሬ​ያ​ማው ቦታ ላይ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።


ብዙ መብል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ቡ​ማ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተአ​ም​ራ​ትን የሠ​ራ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ታመ​ሰ​ግ​ና​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements