Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለአ​ንተ ያዘ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም አጥ​ብ​ቀህ ጠብቅ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዞች፣ ምስክርነቶችና ሥርዐቶች በጥንቃቄ ጠብቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እርሱ ያዘዛችሁንም ትእዛዞች፥ ድንጋጌዎችና ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ለእናንተ ያዘዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ምስክሩንም ሥርዓቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 6:17
15 Cross References  

እንደ በረሃ ቋያ የኀ​ያል ፍላ​ጾች የተ​ሳሉ ናቸው።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፤


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤


እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


ነገር ግን ሁላ​ች​ሁም በዚች ተስ​ፋ​ችሁ እን​ዲሁ ትጋ​ታ​ች​ሁን እስከ መጨ​ረ​ሻው ታሳዩ ዘንድ እን​ወ​ዳ​ለን።


“እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥


ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላ​ካ​ችሁ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ችሁ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእ​ር​ሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አት​በሉ።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ዛሬ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ትእ​ዛዝ ታደ​ርጉ ዘንድ ዕወቁ፤


ከዐ​መ​ፀኛ ከን​ፈር፥ ከሸ​ን​ጋ​ይም አን​ደ​በት፥ አቤቱ፥ ነፍ​ሴን አድ​ናት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements