ዘዳግም 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9-10 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኛና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም። See the chapter |