Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 5:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 “በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ና​ን​ተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተ​ና​ገ​ሩ​ህን ቃል ድምፅ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ሩህ ሁሉ ትክ​ክል ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ይህን ስትነግሩኝ እግዚአብሔር ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፤ “ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ያሉትም ሁሉ መልካም ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 “በተናገራችሁኝም ጊዜ ጌታ የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘የዚህን ሕዝብ ነገር፥ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “እግዚአብሔርም፥ ይህን ስትሉኝ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለኝ፤ ‘እነዚህ ሰዎች ለአንተ የተናገሩትን ሁሉ ሰምቻለሁ፤ አባባላቸውም ትክክል ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነገር ነው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 5:28
4 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ለአ​ንተ የተ​ና​ገ​ሩት ሁሉ ልክ ነው።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የዮ​ሴፍ ልጆች ነገድ በእ​ው​ነት ተና​ገሩ።


“የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ።


አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements