Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 5:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በእ​ሳት መካ​ከል ድም​ፁን በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ሲነ​ድድ እና​ንተ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ወደ እኔ ቀረ​ባ​ችሁ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ተራራው በእሳት ሲቃጠል፣ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፣ እናንተ የየነገዶቻችሁ አለቆችና ሽማግሌዎቻችሁም በሙሉ ወደ እኔ ዘንድ መጣችሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ሁሉ፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ የነገድ አለቆችና መሪዎች ሁሉ ወደ እኔ መጥታችሁ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ተራራው በእሳት ሲነድድ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፤

See the chapter Copy




ዘዳግም 5:23
6 Cross References  

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ፤ በእ​ሳ​ትና በጨ​ለማ፥ በጭ​ጋ​ግና በዓ​ውሎ ነፋስ መካ​ከል ሆኖ በታ​ላቅ ድምፅ እነ​ዚ​ህን ቃሎች ለጉ​ባ​ኤ​ያ​ችሁ ሁሉ ተና​ገረ፤ ምንም አል​ጨ​መ​ረም። በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው፤ ለእ​ኔም ሰጣ​ቸው።


አላ​ች​ሁም፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሩ​ንና ታላ​ቅ​ነ​ቱን አሳ​ይ​ቶ​ናል፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ድም​ፁን ሰም​ተ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰው ጋር ሲነ​ጋ​ገር፥ ሰው​ዬው በሕ​ይ​ወት ሲኖር ዛሬ አይ​ተ​ናል።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን፦ ‘እን​ዳ​ን​ሞት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ደግሞ አን​ስማ፤ ይህ​ችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላ​ችሁ እንደ ለመ​ና​ች​ሁት ሁሉ።


እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements