| ዘዳግም 31:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እግዚአብሔር አምላክም ባጠፋቸው በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁለቱ በአሞሬዎናውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ፥ በምድራቸውም እንዳደረገ እንዲሁ ያደርግባቸዋል።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው፣ እነዚህንም ያጠፋቸዋል።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታ የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል።See the chapter አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንንና ዖግን ድል ነሥቶ አገራቸውን እንዳጠፋ ሁሉ በእነርሱም ላይ እንዲሁ ያደርጋል።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔርም ባጠፋቸው በአሞራውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ በምድራቸውም እንዳደረገ ያደርግባቸዋል።See the chapter |