Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ነገር ግን እጅግ ከብ​ቶች እን​ዳ​ሉ​አ​ችሁ አው​ቃ​ለ​ሁና ሴቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋ​ችሁ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሆኖም ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ፣ (ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁም ስለማውቅ) ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቈዩ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ነገር ግን፥ ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁና፥ ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀራሉ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ብዙ ከብት እንዳላችሁ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እዚህ መቅረት የሚችሉት ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ ናቸው፤ ስለዚህም እነርሱን እኔ በሰጠኋችሁ ከተሞች ወደ ኋላ ትታችሁ ትሄዳላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ነገር ግን እጅግ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁና ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤

See the chapter Copy




ዘዳግም 3:19
4 Cross References  

ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።


ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው።


ወደ እር​ሱም ቀር​በው አሉት፥ “በዚህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ችን በረ​ቶ​ችን፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንም ከተ​ሞ​ችን እን​ሠ​ራ​ለን፤


ልጆ​ቻ​ችን ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ እን​ሰ​ሶ​ቻ​ች​ንም ሁሉ በዚያ በገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements