Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዓረባንም፥ ከዮርዳኖስ ጋር እንደ ወሰን፥ ከኪኔሬት እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ፥ የጨው ባሕር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን ያካትታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በስተ ምዕራብ በኩል ያለው ግዛታቸው አራባን ዮርዳኖስንና በአካባቢው ያለውን ምድር ያጠቃልላል፤ በስተምሥራቅ በኩል ከገሊላ ባሕር በፒስጋ ተራራ ግርጌ እስካለው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ይደርሳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከኪኔሬት እስከ ዓረባ ባሕር እርሱም የጨው ባሕር ድረስ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን ዓረባ ዮርዳኖስንም ዳሩንም ሰጠኋቸው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 3:17
16 Cross References  

በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለ​ውን ዓረባ እስከ ኬኔ​ሬት ባሕር ድረስ፥ በአ​ሴ​ሞት መን​ገድ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ከፋ​ስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለ​ውን ምድር የገ​ዛው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ሴዎን፤


እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ መሿ​ለ​ኪያ ካለው ከአ​ሴ​ዶን ተራራ በታች ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ።


የድ​ን​በ​ራ​ቸ​ውም ፍጻሜ በሰ​ሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደ​ር​ሳል፤ በደ​ቡ​ብም በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ዮር​ዳ​ኖስ ነው። ይህም በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በር ነው።


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ነበረ። በሰ​ሜ​ንም በኩል ያለው ድን​በር በዮ​ር​ዳ​ኖስ መጨ​ረሻ እስ​ካ​ለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤


በደ​ቡ​ብም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስ​ከ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ነበረ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ቤት​ሀ​ራም፥ ቤት​ን​ምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ቅሬታ ነበረ። ድን​በ​ሩም ዮር​ዳ​ኖ​ስና በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የኬ​ኔ​ሬት ባሕር ወዲ​ያ​ኛው ዳርቻ ነበረ።


በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።


ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።


የተ​መ​ሸ​ጉ​ትም የሲ​ዶና ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ጤሮስ፥ አማ​ታ​ዳ​ቄት፥ ቄሬት፥


በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ ገሊላ ይወ​ጣል፤ ወደ ዓረ​ባም ይወ​ር​ዳል፤ ወደ ባሕ​ሩም ይገ​ባል፤ ወደ ባሕ​ሩም ወደ ረከ​ሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃ​ውን ይፈ​ው​ሰ​ዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements