Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 27:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ከእ​ን​ጀራ እናቱ ጋር የሚ​ተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረት ገል​ጦ​አ​ልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ከአባቱ ሚስት ጋራ የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ሚስት ገልቧልና የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ ‘የአባቱ ሚስቶች ከሆኑት ከየትኛዋም ጋር ግንኙነት በማድረግ የአባቱን ክብር የሚያዋርድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ልብስ ገልጦአልና ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 27:20
12 Cross References  

“ማና​ቸ​ውም ሰው የእ​ን​ጀራ እና​ቱን አይ​ው​ሰድ፤ የአ​ባ​ቱ​ንም ኀፍ​ረት አይ​ግ​ለጥ።


የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነው።


በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና።


ማና​ቸ​ውም ሰው ከአ​ባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአ​ባ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አል፤ ሁለ​ቱም ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።


የድ​ሆ​ችን ራስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ የት​ሑ​ታ​ን​ንም ፍርድ ያጣ​ም​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም ያረ​ክሱ ዘንድ አባ​ትና ልጁ ወደ አን​ዲት ሴት ይገ​ባሉ፤


በአ​ንቺ ውስጥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአ​ን​ቺም ውስጥ አደፍ ያለ​ባ​ትን አዋ​ረዱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም በኵር የሮ​ቤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። እርሱ የበ​ኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምን​ጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስ​ራ​ኤል በረ​ከ​ቱን ለልጁ ለዮ​ሴፍ ሰጠ፤ ብኵ​ር​ናም አል​ተ​ቈ​ጠ​ረ​ለ​ትም።


ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም በሰ​ገ​ነት ላይ ድን​ኳን ተከ​ሉ​ለት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባ​ቶች ገባ።


እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


የአ​ባ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋና የእ​ና​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ እና​ትህ ናትና ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።


“ፍሬ ዘሩ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተ​ቈ​ረጠ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements