Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፣ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ ቤቱ ይቈይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “አዲስ ሚስት ያገባ ሰው ወታደር ሆኖ ለማገልገል አይገደድ፤ ሌላም ተጽዕኖ አይደረግበት፤ ለአንድ ዓመት ከማናቸውም ግዴታ ነጻ ሆኖ በቤቱ ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ፥ ነገርም አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ፥ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

See the chapter Copy




ዘዳግም 24:5
12 Cross References  

የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ ከልጅነት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።


ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።


ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


በሕ​ይ​ወ​ትህ፥ አን​ተም ከፀ​ሓይ በታች በም​ት​ደ​ክ​ም​በት ድካም ይህ ዕድል ፈን​ታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀ​ሓይ በታች በሰ​ጠህ፥ በከ​ንቱ ዘመ​ንህ ሁሉ፥ ከም​ት​ወ​ድ​ዳት ሚስ​ትህ ጋር ደስ ይበ​ልህ።


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።


“የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements