Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሰ​ደ​ዳት የቀ​ድሞ ባልዋ ከረ​ከ​ሰች በኋላ ደግሞ ያገ​ባት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ ያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠላ ነውና፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር አታ​ር​ክስ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በሁለቱም መንገድ ቢሆን ያ የመጀመሪያ ባልዋ እንደገና ሊያገባት አይፈቀድለትም፤ እንደ ረከሰች አድርጎ ይቊጠራት፤ እርስዋን እንደገና ቢያገባ ይህ ድርጊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ እንደዚህ ያለውን አስከፊ ኃጢአት መፈጸም አይገባችሁም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 24:4
6 Cross References  

“ሰው ሚስ​ቱን ቢፈታ፥ ከእ​ር​ሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችን? ያች ሴት እጅግ የረ​ከ​ሰች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? አን​ቺም ከብዙ እረ​ኞች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ወደ እኔም ትመ​ለ​ሻ​ለ​ሽን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ባል ቢጠ​ላት፥ የፍ​ች​ዋ​ንም ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ቢሰ​ጣት ፥ ከቤ​ቱም ቢሰ​ድ​ዳት፥ ወይም ሚስት አድ​ርጎ ያገ​ባት ሁለ​ተ​ኛው ባልዋ ቢሞት፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements