Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 24:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ወይም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከአ​ሉት መጻ​ተ​ኞች ድሃና ችግ​ረኛ የሆ​ነ​ውን ምን​ደኛ ደመ​ወ​ዙን አት​ከ​ል​ክ​ለው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ችግረኛና ድኻ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድምህም ሆነ፣ ከከተሞችህ በአንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዘው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድምህም ሆነ፥ ከከተሞችህ በአንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዘው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እስራኤላዊውም ሆነ ወይም ከአገርህ ከተማዎች በአንዱ የሚኖር የውጪ አገር ተወላጅ ድኻና ችግረኛ ሆኖ የተቀጠረውን ማናቸውንም ሰው አትበዝብዘው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ድሀና ችግረኛ የሆነውን ምንደኛ፥ ከወንድሞችህ ወይም በምድርህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚቀመጡት መጻተኞች ቢሆን፥ አታስጨንቀው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 24:14
15 Cross References  

ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤ ፈጣሪውን የሚያከብር ግን ለድሃ ምሕረትን ያደርጋል።


ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ በችግሩ ጊዜም ለባለጠጋ ይሰጣል።


በሰ​ማ​ርያ ተራራ የም​ት​ኖሩ፥ ድሆ​ች​ንም የም​ት​በ​ድሉ፥ ችግ​ረ​ኞ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጌቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፦ አምጡ እን​ጠጣ የም​ትሉ እና​ንተ የባ​ሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ።


የድ​ሆ​ችን ራስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ የት​ሑ​ታ​ን​ንም ፍርድ ያጣ​ም​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ስም ያረ​ክሱ ዘንድ አባ​ትና ልጁ ወደ አን​ዲት ሴት ይገ​ባሉ፤


ችግ​ረ​ኛ​ውን በጥ​ዋት የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ድሃ የም​ት​ቀሙ እና​ንተ ሆይ!


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


መጽሐፍ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፤” ደግሞ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል፤” ይላልና።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ካሉ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ከሚ​ኖሩ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ አንዱ ቢቸ​ገር ልብ​ህን አታ​ጽና፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ከመ​ስ​ጠት እጅ​ህን አት​መ​ልስ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements