Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 24:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ለብ​ሶት እን​ዲ​ተኛ እን​ዲ​ባ​ር​ክ​ህም ፀሐይ ሳይ​ገባ መያ​ዣ​ውን ፈጽ​መህ መል​ስ​ለት፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምጽ​ዋት ይሆ​ን​ል​ሃል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቈጠርልሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርልሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለብሶት ያድር ዘንድ ፀሐይ ሳትጠልቅ መልስለት፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለብሶት እንዲተኛ እንዲባርክህም ፀሐይ ሳይገባ መያዣውን ፈጽመህ መልስለት፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ይሆንልሃል።

See the chapter Copy




ዘዳግም 24:13
24 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብን​ጠ​ብቅ ለእኛ ምሕ​ረት ይሆ​ን​ል​ናል።”


ድሃ ነውና፥ ተስ​ፋ​ውም እርሱ ነውና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ጮ​ኽ​ብህ፥ ኀጢ​አ​ትም እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ደመ​ወ​ዙን ፀሐይ ሳይ​ገባ በቀኑ ስጠው።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


ተቈጡ፤ አት​በ​ድ​ሉም፤ ፀሐይ ሳይ​ጠ​ል​ቅም ቍጣ​ች​ሁን አብ​ርዱ።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም መያ​ዣን ቢመ​ልስ፥ የነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ቢከ​ፍል፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ትእ​ዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢ​አ​ትም ባይ​ሠራ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥


ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤


ያን ጊዜ ብር​ሃ​ንህ እንደ ንጋት ይበ​ራል፤ ፈው​ስ​ህም ፈጥኖ ይወ​ጣል፤ ጽድ​ቅ​ህም በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይጋ​ር​ድ​ሃል።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


አብ​ራ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።


ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​ወ​ስድ፥ ባይ​ቀ​ማም፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ ለተ​ራ​ቈ​ተ​ውም ልብ​ስን ቢያ​ለ​ብስ፥


ያም ሰው ድሃ ቢሆን መያ​ዣ​ውን በአ​ንተ ዘንድ አታ​ሳ​ድር።


“ከአ​ንተ ጋር ለተ​ቀ​መ​ጠው ለድ​ሃው ወገ​ንህ ብር ብታ​በ​ድ​ረው፥ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ አራ​ጣም አታ​ስ​ከ​ፍ​ለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements