Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “የወ​ን​ድ​ምህ በሬ ወይም በግ በመ​ን​ገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አት​በል፤ እነ​ር​ሱን መል​ሰህ ለወ​ን​ድ​ምህ ስጥ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፥ ወደ ወንድምህ መልሰው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “የእስራኤላዊ ወገንህ ንብረት የሆነ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታገኝ ዝም ብለህ አትለፈው፤ ወደ ባለቤቱ መልሰህ ውሰድለት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ ወደ ወንድምህ መልሰው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 22:1
21 Cross References  

የጠ​ፋ​ው​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የደ​ከ​መ​ው​ንም አጸ​ና​ለሁ፤ የወ​ፈ​ረ​ው​ንና የበ​ረ​ታ​ው​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ በፍ​ር​ድም እጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።


ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ የሚገደሉትንም መዋረዳቸውን ቸል አትበል።


እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


እርሱም መልሶ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፤” አለ።


ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።


የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።


ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ፊቱን የመ​ለ​ሰ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፥ እተ​ማ​መ​ን​በ​ት​ማ​ለሁ።


ዘሩ​ንም ለሞ​ሎክ ሲሰጥ፥ የሀ​ገሩ ሕዝብ ያን ሰው ቸል ቢሉት፥ አይ​ተው እን​ዳ​ላዩ ቢሆኑ፥ ባይ​ገ​ድ​ሉ​ትም፥ እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ።


“እህ​ል​ህን በም​ታ​በ​ራ​ይ​በት ጊዜ የበ​ሬ​ውን አፉን አት​ሰ​ረው።” እን​ግ​ዲህ ይህን የጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሬ አሳ​ዝ​ኖት ነውን?


ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥


ወን​ድ​ም​ህም በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያህ ባይ​ሆን ወይም ባታ​ው​ቀው ይዘ​ሃ​ቸው ወደ ቤትህ ትገ​ባ​ለህ፤ ወን​ድ​ምህ እስ​ኪ​ሻ​ቸው ድረስ በአ​ንተ ዘንድ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ለእ​ር​ሱም ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለህ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements