Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለል​ጆቹ ከብ​ቱን በሚ​ያ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት በተ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵሩ ፊት ከተ​ወ​ደ​ደ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ልጅ በኵር ያደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፣ የብኵርናን መብት ከማይወድዳት ሚስቱ ከወለደው በኵር ልጅ ገፎ፣ ከሚወድዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ፥ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ፥ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ታዲያ፥ ያ ሰው ሀብቱንና ንብረቱን ለልጆቹ በሚያካፍልበት ጊዜ ለበኲር ልጁ ሊሰጥ የሚገባውን ድርሻ በተለይ ከሚያፈቅራት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በመስጠት አድልዎ ማድረግ አይገባውም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኩሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኩር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤

See the chapter Copy




ዘዳግም 21:16
10 Cross References  

ከሜ​ራ​ሪም ልጆች ለነ​በ​ረው ለሖሳ ፊተ​ኛ​ውን በር የሚ​ጠ​ብቁ ልጆች ነበ​ሩት፤ አለ​ቃ​ውም ሰምሪ ነበረ፤ በኵር አል​ነ​በ​ረም፤ አባቱ ግን አለቃ አደ​ረ​ገው፤


ይሁ​ዳም በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል በረታ፥ አለ​ቃም ከእ​ርሱ ሆነ፤ በረ​ከት ግን ለዮ​ሴፍ ነበረ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ።


ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


አባ​ታ​ቸ​ውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕቃ፥ በይ​ሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ግን የበ​ኵር ልጁ ስለ​ሆነ ለኢ​ዮ​ራም ሰጠው።


ያዕ​ቆ​ብም ዔሳ​ውን፥ “ዛሬ ብኵ​ር​ና​ህን ስጠኝ” አለው።


“ለአ​ንድ ሰው አን​ዲቱ የተ​ወ​ደ​ደች፥ አን​ዲ​ቱም የተ​ጠ​ላች ሁለት ሚስ​ቶች ቢኖ​ሩት፥ ለእ​ር​ሱም የተ​ወ​ደ​ደ​ችው፥ ደግ​ሞም የተ​ጠ​ላ​ችው ልጆ​ችን ቢወ​ልዱ፥ በኵ​ሩም ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ ቢሆን፥


ነገር ግን ከከ​ብቱ ሁለት እጥፍ ለእ​ርሱ በመ​ስ​ጠት ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስ​ታ​ውቅ። የኀ​ይሉ መጀ​መ​ሪያ ነውና በኵ​ር​ነቱ የእ​ርሱ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements