Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም አለቆቹ፣ “የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ” በማለት ጨምረው ይናገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ከዚያም አለቆቹ፥ ‘የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ’ በማለት ጨምረው ይናገሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “የጦር መሪዎች በሌላም በኩል እንዲህ ብለው ይጠይቁ፥ ‘ወኔ የጐደለው ፈሪ ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? እንዲህ ያለ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እንዲህ ያለ ሰው የሌሎችን ወኔ ያቀዘቅዛል፤’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አለቆቹም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ድንጉጥ ሰው ቢሆን እርሱ ፈርቶ የወንድሞቹን ልብ ደግሞ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 20:8
14 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማንም ዕርፍ ይዞ እያ​ረሰ ወደ ኋላው የሚ​መ​ለ​ከት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የተ​ገባ አይ​ሆ​ንም” አለው።


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰው​ነ​ት​ህን ጠብቅ።


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።


ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ክፉ ነገር መል​ካም ጠባ​ይን ያበ​ላ​ሻ​ልና።


ጸሐ​ፍ​ቱም ለሕ​ዝቡ ነግ​ረው በጨ​ረሱ ጊዜ ከታ​ላ​ላቁ ሕዝብ መካ​ከል የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆ​ችን ይሹሙ።


በመከራ ቀንና በክፉ ቀን እስኪያልቅ ድረስ ያረክሰዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements