Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ዘምዙማውያን ብርቱዎች፣ ቍጥራቸው የበዛና እንደ ዔናቃውያን ቁመተ ረዣዥሞች ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱም አሳደዷቸው፤ በምትካቸውም ሰፈሩበት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፥ ጌታ ከፊታቸው አጠፋቸው፥ እነርሱንም ቀምተዋቸው በስፍራቸው ተቀመጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እነርሱም እንደ ዐናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች፥ ብርቱና ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ዐሞናውያን ስለ ደመሰሱአቸው ምድራቸውን ወርሰው ራሳቸው ሰፍረውበት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 2:21
8 Cross References  

አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


ያም ደግሞ የራ​ፋ​ይም ምድር ተብሎ ተቈ​ጠረ፤ ራፋ​ይ​ምም አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበረ፤ አሞ​ና​ው​ያን ግን “ዘም​ዞ​ማ​ው​ያን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements