Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው በዚያ ስፍራ ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ህ​በት ወራት፥ ፀሐይ ሲገባ፥ ማታ ፋሲ​ካን ትሠ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ነገር ግን ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ፣ ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱ ላይ ከግብጽ በወጣህበት ሰዓት፣ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ነገር ግን አምላክህ ጌታ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ፥ ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ነገር ግን የመሥዋዕቱን እንስሳ የምታርደው እግዚአብሔር አምላክህ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ ነው። ይኸውም ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ በመረጠው በዚያ ስፍራ ከግብፅ በወጣህበት ወራት፥ ፀሓይ ሲገባ፥ ማታ ፋሲካን ሠዋ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 16:6
10 Cross References  

ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


ይህስ ባይ​ሆን ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓ​ለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመ​ሠ​ዋት ኀጢ​አ​ትን ይሽ​ራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገ​ለጠ።


በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።


በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድ​ር​ጉት፤ ከቂጣ እን​ጀ​ራና ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊ​ዜው አድ​ር​ጉት፤ እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ እንደ ፍር​ዱም ሁሉ አድ​ር​ጉት።”


ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በማ​ን​ኛ​ዪ​ቱም ፋሲ​ካን ትሠዋ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements