Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሰባት ቀንም በሀ​ገ​ርህ ሁሉ የቦካ አይ​ታ​ይም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማታ ከሠ​ዋ​ኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይ​ደር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማንኛውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምድርህ በማንኛውም ሰው ቤት እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ቀን ማታ ለመሥዋዕት የታረደው እንስሳ ሥጋው በሙሉ በዚያው ሌሊት ተበልቶ ማለቅ አለበት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሰባት ቀንም በአገርህ ሁሉ እርሾ አይታይም፤ በመጀመሪያው ቀን ማታ ከሠዋኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይደር።

See the chapter Copy




ዘዳግም 16:4
9 Cross References  

“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር።


ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት አን​ዳች አታ​ስ​ቀሩ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም ከእ​ርሱ አት​ስ​በሩ፤ ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት የተ​ረፈ ቢኖር በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት።


ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ እርሾ ያለ​በት እን​ጀራ አይ​ታይ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ እርሾ አይ​ኑር።


“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ።


በእ​ሳ​ትም የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ሥጋ​ውን በዚ​ያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣ​ውን እን​ጀ​ራም ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የበ​ዓ​ሌም ስብ እስ​ኪ​ነጋ አይ​ደር።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በማ​ን​ኛ​ዪ​ቱም ፋሲ​ካን ትሠዋ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements