Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 16:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በሕ​ይ​ወት ትኖር ዘንድ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሰ​ጥ​ህን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ተከ​ተል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ የጽድቅ ፍርድን ብቻ ተከተል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በሕይወት እንድትኖርና ጌታ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ትክክለኛ፥ እውነተኛውንም ፍርድ ብቻ ተከተል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር ወርሰህ በሕይወት መኖር ትችል ዘንድ ሁልጊዜ ቅንና ትክክለኛ ሁን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሕይወት ትኖር ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም የሚሰጥህን ምድር ትወርስ ዘንድ እውነተኛውን ፍርድ ተከተል።

See the chapter Copy




ዘዳግም 16:20
9 Cross References  

አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ።


ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።


ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?


በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ፤


“አሁ​ንም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ርሱ፥ ዛሬ የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


“ለአ​ንተ በም​ት​ሠ​ራው በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ከማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ አድ​ር​ገህ አት​ት​ከል።


ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements