Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 12:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን በሚ​ታ​ይህ ስፍራ ሁሉ እን​ዳ​ታ​ቀ​ርብ ተጠ​ን​ቀቅ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በፈለግኸው ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሚቃጠል መሥዋዕትህን በማናቸውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን በሚታይህ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 12:13
11 Cross References  

በኮ​ረ​ብታ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች ግን ከእ​ስ​ራ​ኤል አላ​ራ​ቀም። ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እስከ አሁን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘ​መኑ ሁሉ ፍጹም ነበረ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፥ በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ከአ​ንዱ ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ርብ፤ በዚ​ያም ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


በድ​ን​ኳኑ ፊት ካለው ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሌላ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን የሠ​ራ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በማ​መፅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ መከ​ተ​ልን ለመ​ተው በማ​ለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”


እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አል​ተ​ሠ​ራም ነበ​ርና ሕዝቡ በኮ​ረ​ብታ ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


Follow us:

Advertisements


Advertisements