Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበ​ዙም ዘንድ፥ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን የም​ት​ሻ​ገ​ሩ​ላ​ትን ምድር እን​ድ​ት​ወ​ር​ሷት ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፣ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፥ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “እንግዲህ ወደምትወርሱት ምድር ተሻግራችሁ ለመያዝ ኀይል ታገኙ ዘንድ እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8-9 እንግዲህ እንድትጠነክሩ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሻገሩባት ምድር እንድትገቡ እንድትወርሱአትም፥ እግዚአብሔርም ለእነርሱና ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 11:8
19 Cross References  

እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ።


የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ታገ​ባ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል” ብሎ አዘ​ዘው።


ፍለ​ጋ​ዬ​ንና መን​ገ​ዴን አንተ ትመ​ረ​ም​ራ​ለህ፤ መን​ገ​ዶ​ቼን ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ዐወ​ቅህ፥


በፍ​ጹም ኀይል፥ በክ​ብሩ ጽናት፥ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥት፥ በተ​ስ​ፋና በደ​ስ​ታም ጸን​ታ​ችሁ።


“ሁሉን አብ​ዝቶ ስለ ሰጠህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ሥ​ሓና በቀና ልብ አላ​መ​ለ​ክ​ኸ​ው​ምና፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ጋ​ቸ​ውን ታላ​ላቅ ሥራ​ዎች ሁሉ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋ​ልና።


ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር የም​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ያን ጊዜ አዘ​ዘኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements