Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እነዚህም ተራራዎች ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምዕራብ በኩል፥ በአራባ በሚኖሩት በከነዓናውያንም ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት ከሞሬ ዛፍ አጠገብ የሚገኙ ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘዳግም 11:30
6 Cross References  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።


ይህ​ንም ነገር ለኢ​ዮ​አ​ታም በነ​ገ​ሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድም​ፁ​ንም አን​ሥቶ አለ​ቀሰ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “የሰ​ቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይስ​ማ​ችሁ።


ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements