Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በእ​ና​ን​ተም ፊት ማንም መቆም አይ​ች​ልም፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ማስ​ፈ​ራ​ታ​ች​ሁን፥ ማስ​ደ​ን​ገ​ጣ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ረ​ግ​ጡ​አት ምድር ሁሉ ላይ ያኖ​ራል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ ጌታ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በዚያች ምድር በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈሩአችሁ ያደርጋል፤ ሊቋቋማችሁ የሚችልም ከቶ አይገኝም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ እርሱ እንደ ተናገራችሁ፥ ማስፈራታችሁን ማስደንገጣችሁንም በምትረግጡአት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል።

See the chapter Copy




ዘዳግም 11:25
7 Cross References  

በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።


በፊ​ትህ መፈ​ራ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን ሕዝብ ሁሉ አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ እን​ዲ​ሸ​ሹ​ልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።


ከሰ​ማይ በታች ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ማስ​ደ​ን​ገ​ጥ​ህ​ንና ማስ​ፈ​ራ​ት​ህን እሰ​ድድ ዘንድ ዛሬ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ ስም​ህን በሰሙ ጊዜ በፊ​ትህ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ድን​ጋ​ጤም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።


ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና።


የዳ​ዊ​ትም ዝና በየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈ​ራ​ቱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ አደ​ረገ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements