Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እና​ንተ የል​ባ​ች​ሁን ክፋት ግዘሩ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙት፤ ከእንግዲህም ወዲያ ዐንገተ ደንዳና አትሁኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እንግዲህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህም ከአሁን በኋላ ልበ ደንዳናነትንና እልኸኛነትን አስወግዳችሁ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16-17 እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 10:16
13 Cross References  

እና​ን​ተም የይ​ሁዳ ሰዎች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ወጣ የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውም ሳይ​ኖር እን​ዳ​ይ​ነድ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ተገ​ረዙ፤ የል​ባ​ች​ሁ​ንም ሸለ​ፈት አስ​ወ​ግዱ።


በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።


እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤


የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ።


እን​ግ​ዲህ አንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ነህና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መል​ካም ምድር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠህ ስለ ጽድ​ቅህ እን​ዳ​ይ​ደለ ዛሬ ዕወቅ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ትድኚ ዘንድ ልብ​ሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚ​ኖ​ር​ብሽ እስከ መቼ ነው?


እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም እን​ዲህ ብዬ ነገ​ር​ሁህ፤ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ እንደ ሆነ አይ​ች​አ​ለሁ፤


የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ቍል​ፈት ትገ​ረ​ዛ​ላ​ችሁ፤ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ላለ​ውም ቃል ኪዳን ምል​ክት ይሆ​ናል።


እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።


አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements