Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘዳግም 1:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ በስ​ተ​ቀር፥ እርሱ ግን ያያ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ተከ​ት​ሎ​አ​ልና የረ​ገ​ጣ​ትን ምድር ለእ​ርሱ፥ ለል​ጆ​ቹም እሰ​ጣ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከይፉኔ ልጅ ከካሌብ በቀር፤ እርሱ ያያታል፥ የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ፥ ምክንያቱም ጌታን ፈጽሞ ተከትሎአል።’

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ወደዚያች ምድር መግባት የሚችል የይፉኔ ልጅ ካሌብ ብቻ ነው፤ እርሱ በፍጹም ልቡ ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ ያቺን የጐበኛትን ምድር ለእርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ ብሎ ማለ።

See the chapter Copy




ዘዳግም 1:36
10 Cross References  

ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


ካሌ​ብም ሕዝ​ቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰ​ኘና፥ “አይ​ደ​ለም! ማሸ​ነ​ፍን እን​ች​ላ​ለ​ንና እን​ውጣ፤ እን​ው​ረ​ሳት” አለ።


ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፤


የሰ​ዎ​ቹም ስም ይህ ነው፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፥


ሰም​ተው ያሳ​ዘ​ኑ​ትስ እነ​ማን ናቸው? በሙሴ እጅ ከግ​ብፅ የወ​ጡት ሁሉ አይ​ደ​ሉ​ምን?


አን​ደ​በ​ታ​ቸው በላ​ያ​ቸው ደከመ፥ የሚ​ያ​ዩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ደነ​ገጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements