Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ቈላስይስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በውጭ ካሉት ሰዎች ጋራ ባላችሁ ግንኙነት በጥበብ ተመላለሱ፤ በተገኘውም ዕድል ሁሉ ተጠቀሙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በማንኛውም አጋጣሚ ጊዜ እየተጠቀማችሁ በማያምኑት ሰዎች ዘንድ በጥበብ ኑሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።

See the chapter Copy




ቈላስይስ 4:5
15 Cross References  

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።


መታ​ዘ​ዛ​ች​ሁም በሁሉ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል፤ እኔም በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ናል፤ ለመ​ል​ካም ነገር ጠቢ​ባን፥ ለክፉ ነገ​ርም የዋ​ሃን እን​ድ​ት​ሆኑ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።


በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።


እግ​ር​ህም በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ት​ሰ​ና​ከል በእ​ጆ​ቻ​ቸው ያነ​ሡ​ሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements