Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ቈላስይስ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አሮ​ጌ​ውን ሰው ከሥ​ራው ጋር ተዉት እንጂ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አቷሹ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋራ አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁ አስወግዳችሁታልና እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አሮጌውን ባሕርይ ከነሥራው አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁት እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥

See the chapter Copy




ቈላስይስ 3:9
16 Cross References  

ስለ​ዚ​ህም ሐሰ​ትን ተዉ​አት፤ ሁላ​ች​ሁም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር እው​ነ​ትን ተነ​ጋ​ገሩ፤ እኛ አንድ አካል ነንና።


የቀ​ድሞ ጠባ​ያ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ይህ​ንም ስሕ​ተት በሚ​ያ​መ​ጣው ምኞት ስለ​ሚ​ጠ​ፋው ስለ አሮ​ጌው ሰው​ነት እላ​ለሁ።


“አት​ስ​ረቁ፤ አት​ዋ​ሹም፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም የሚ​ቀማ አይ​ኑር።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


ነገር ግን የኀ​ጢ​አ​ትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ለው አሮ​ጌው ሰው​ነ​ታ​ችን እንደ ሆነ ይህን እና​ው​ቃ​ለን፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ዳግ​መና ለኀ​ጢ​አት እን​ገዛ ዘንድ አን​መ​ለ​ስም።


የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፣ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።


ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


አሁ​ንም ቍጣ​ንና ብስ​ጭ​ትን፥ ክፋ​ት​ንና ስድ​ብን፥ የሚ​ያ​ሳ​ፍ​ረ​ው​ንም ነገር ተዉ፤ ከንቱ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


እር​ሱም፥ “ሕዝቤ ልጆች አይ​ደ​ሉ​ምን? ካል​ከ​ዱ​ኝስ ከመ​ከ​ራ​ቸው ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ።


የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣


ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements