Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ቈላስይስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የገዦችና የባለሥልጣናትንም ማዕርግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ በመስቀሉ ድል በመንሣት እነርሱን በይፋ አጋለጣቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኀይሎችንና ባለሥልጣኖችን በመስቀሉ ድል ነሥቶ ትጥቃቸውን ካስፈታ በኋላ ምርኮኞች ሆነው በይፋ እንዲታዩ አደረጋቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።

See the chapter Copy




ቈላስይስ 2:15
25 Cross References  

ልጆች በሥ​ጋና በደም አንድ ናቸ​ውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እንደ ወን​ድም ሆነ​ላ​ቸው፤ መል​አከ ሞትን በሞቱ ይሽ​ረው ዘንድ፥ ይኸ​ውም ሰይ​ጣን ነው።


“ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።


ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።


ስለ ፍር​ድም፥ የዚህ ዓለም ገዢ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታ​ልና ነው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰይ​ጣ​ንን ከሰ​ማይ እንደ መብ​ረቅ ሲወ​ድቅ አየ​ሁት።


ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።


ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤


ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሆም​ጣ​ጤ​ውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈ​ጸመ” አለ፤ ራሱ​ንም አዘ​ን​ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ መን​ግ​ሥ​ቱን እጅ ባደ​ረገ ጊዜ፥ ገዥም ሁሉ፥ ንጉ​ሥም ሁሉ፥ ኀይ​ልም ሁሉ በተ​ሻረ ጊዜ፥ ያን​ጊዜ ፍጻሜ ይሆ​ናል።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘወ​ትር ድል በመ​ን​ሣቱ የሚ​ጠ​ብ​ቀን፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ የዕ​ው​ቀ​ቱን መዓዛ በእኛ የሚ​ገ​ልጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ብዙ ልዩ ልዩ የሆ​ነች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኩል በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለ​ቆ​ችና ሥል​ጣ​ናት ትታ​ወቅ ዘንድ፤


እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements