Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ቈላስይስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በቈ​ላ​ስ​ይስ ላሉ ቅዱ​ሳ​ንና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በቈላስይስ ለሚኖሩ፣ በክርስቶስ ለሆኑ ቅዱሳንና ታማኝ ወንድሞች፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በቈላስይስ ለሚኖሩ፥ በክርስቶስ ቅዱሳንና ታማኞች ለሆኑ አማኞች፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በቍኦላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፦ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን።

See the chapter Copy




ቈላስይስ 1:2
14 Cross References  

የመለኮቱ ኀይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከሆነ ከጳ​ው​ሎስ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላመኑ በኤ​ፌ​ሶን ላሉ ቅዱ​ሳን፥


በሮሜ ላላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዳ​ችሁ፥ ለመ​ረ​ጣ​ች​ሁና ላከ​በ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።


በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለከ​በ​ሩና ቅዱ​ሳን ለተ​ባሉ የእ​ነ​ር​ሱና የእኛ ጌታ የሆ​ነ​ውን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ስም በየ​ስ​ፍ​ራው ለሚ​ጠሩ ሁሉ፥


ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር፥ ከሙታንም በኵር፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።


እና​ን​ተም ዜና​ዬን እን​ድ​ታ​ውቁ የም​ን​ወ​ደው ወን​ድ​ማ​ችን የታ​መነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ቲኪ​ቆስ የም​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያስ​ረ​ዳ​ች​ኋል።


በሌ​ሊ​ትም ጐበ​ኘ​ኸኝ፤ ልቤ​ንም ፈተ​ን​ኸው፥ ፈተ​ን​ኸኝ፥ ዐመ​ፅም አል​ተ​ገ​ኘ​ብ​ኝም።


ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።


አሁ​ንም የሚ​ያ​ምኑ ከአ​መ​ነው ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ይባ​ረ​ካሉ።


ስለ​ዚ​ህም በየ​ስ​ፍ​ራው በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ የሄ​ድ​ሁ​በ​ትን መን​ገድ ይገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መ​ነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞ​ቴ​ዎ​ስን ልኬ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሐና​ንያ ግን መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ሰው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በቅ​ዱ​ሳ​ኖ​ችህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰም​ቻ​ለሁ።


ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements