Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




አሞጽ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ሺህ ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ መቶ ይቀ​ራሉ፤ መቶም ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዐሥር ይቀ​ራሉ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ ሺሕ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣ አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤ አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ “ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት ዐሥር ይቀርላታል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከአንዲት የእስራኤል ከተማ ሺህ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ በሕይወት የሚቀሩት ግን አንድ መቶ ብቻ ይሆናሉ፤ ከሌላይቱም ከተማ መቶ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ ተመልሰው የሚመጡት ግን ዐሥር ብቻ ይሆናሉ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት አሥር ይቀርላታል።

See the chapter Copy




አሞጽ 5:3
10 Cross References  

ኢሳ​ይ​ያ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ስለ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቍጥ​ራ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆ​ንም የተ​ረ​ፉት ይድ​ናሉ።


በሚ​ሄ​ዱ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ መካ​ከል ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይና​ገሩ ዘንድ ከሰ​ይ​ፍና ከራብ፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርም ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችን ከእ​ነ​ርሱ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀ​ሩት ይድ​ናሉ።


በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ዐሥ​ረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ቅጠ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በረ​ገፉ ጊዜ እንደ ግራ​ርና እንደ ኮም​በል ዛፍ ሁነው ይቀ​ራሉ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ከብ​ዛ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት የነ​በ​ረው ቍጥ​ራ​ችሁ ጥቂት ሆኖ ይቀ​ራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ዐሥር ሰዎች በአ​ንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነ​ርሱ ይሞ​ታሉ፤ የቀ​ሩት ግን ይተ​ር​ፋሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲያ​ጠ​ፋህ፥ ሲያ​ፈ​ር​ስ​ህም ደስ ይለ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ትም ዘንድ ከም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ትነ​ቀ​ላ​ለህ ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements