Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በግ​ብፅ ያሉ​ትን የወ​ገ​ኖ​ችን መከራ ማየ​ትን አይ​ቻ​ለሁ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለሁ፤ ላድ​ና​ቸ​ውም ወር​ጃ​ለሁ፤ አሁ​ንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላ​ክህ።’

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ መልሼ እልክሃለሁ።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በግብጽ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ እልክሃለሁ፤’ አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጽኑ መከራ በእርግጥ አይቼአለሁ፤ የጭንቀት ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ላድናቸው ወርጃለሁ፤ አሁንም ና! እኔ አንተን ወደ ግብጽ እልክሃለሁ።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ’ አለው።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 7:34
21 Cross References  

ከሰ​ማይ የወ​ረ​ድሁ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ፥ ፈቃ​ዴን ላደ​ርግ አይ​ደ​ለ​ምና።


“በግ​ብ​ጽም ሳሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አየህ፤ በኤ​ር​ትራ ባሕ​ርም ሳሉ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማህ፤


ሕዝ​ቡም አመኑ፤ ደስም አላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ ጭን​ቀ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ቶ​አ​ልና፤ ሕዝ​ቡም ራሳ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ነገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “ያለና የሚ​ኖር እኔ ነኝ፤ እን​ዲህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ‘ያለና የሚ​ኖር’ ወደ እና​ንተ ላከኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ።


ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም።


የቅ​ድ​ስ​ና​ህ​ንም ክብር ታላ​ቅ​ነት ይና​ገ​ራሉ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።


እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው። በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን ባስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ስ​ፍኑ ጋር ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ዋ​ጉ​አ​ቸው ሰዎች ፊት ከመ​ከ​ራ​ቸው የተ​ነሣ ይቅር ብሏ​ቸ​ዋ​ልና በመ​ስ​ፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አዳ​ና​ቸው።


እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈ​ጽ​ሙ​አት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ባይ​ሆን አው​ቃ​ለሁ።”


ኑ እን​ው​ረድ፤ አንዱ የሌ​ላ​ውን ነገር እን​ዳ​ይ​ሰ​ማው ቋን​ቋ​ቸ​ውን በዚያ እን​ደ​ባ​ል​ቀው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ልጆች የሠ​ሩ​ትን ከተ​ማና ግንብ ለማ​የት ወረደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements