Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከል አቁመው፣ “ይህን ያደረጋችሁት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነርሱንም በመካከል አቁመው “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት በመካከላቸው አቁመው፥ “ይህን ያደረጋችኹት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 4:7
12 Cross References  

ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


“እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


እሺም አሰ​ኛ​ቸው፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ጠር​ተው ገረ​ፉ​አ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም በኢ​የ​ሱስ ስም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ገሥ​ጸው ተዉ​አ​ቸው።


አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ምን ምል​ክት ታሳ​ያ​ለህ?” አሉት።


እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።


ወን​ድ​ሙን የሚ​በ​ድ​ለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አን​ተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደ​ረ​ገህ? ወይስ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ትና​ንት እንደ ገደ​ል​ኸው ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእ​ው​ነት ይህ ነገር ታው​ቆ​አ​ልን?” ብሎ ፈራ።


እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በዝ​ሙት የተ​ያ​ዘች ሴት ወደ እርሱ አም​ጥ​ተው በመ​ካ​ከል አቆ​ሙ​አት።


ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements