Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 4:12
19 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


ነገር ግን ከተ​መ​ሠ​ረ​ተው በቀር ሌላ መሠ​ረት ሊመ​ሠ​ርት የሚ​ችል የለም፤ መሠ​ረ​ቱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።


በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።


ንስ​ሓና የኀ​ጢ​ኣት ስር​የት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጀምሮ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ሰ​በክ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አል።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


እን​ግ​ዲህ ከሰ​ማ​ች​ሁት ከሰ​ማይ በታች በመ​ላው ዓለም ከተ​ሰ​በ​ከው እኔ ጳው​ሎ​ስም አዋጅ ነጋ​ሪና መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ ከተ​ሾ​ም​ሁ​ለት፥ ከወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ተስፋ የመ​ሠ​ረ​ታ​ችሁ አቅ​ዋም ሳይ​ና​ወጥ ጨክ​ና​ችሁ በሃ​ይ​ማ​ኖት ብት​ጸኑ፥


የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።


ከሰ​ማይ በታች ካሉ አሕ​ዛብ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ደጋግ የአ​ይ​ሁድ ሰዎች ነበሩ።


ውኃ​ውም በም​ድር ላይ እጅግ በጣም አሸ​ነፈ፤ ከሰ​ማይ በታች ያሉ ረዣ​ዥም ተራ​ሮ​ችን ሁሉ ሸፈነ።


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements