Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እር​ሱም መል​ካም በም​ት​ባ​ለው በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ምጽ​ዋት ይለ​ምን የነ​በ​ረው እንደ ሆነ ዐወ​ቁት፤ በእ​ር​ሱም ከሆ​ነው የተ​ነሣ መገ​ረ​ምና መደ​ነቅ ሞላ​ባ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህ ሰው ቀደም ሲል “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በርሱ ላይ ከተፈጸመውም ነገር የተነሣ በመደነቅና በመገረም ተሞሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “መልካም” በሚሉአትም በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ውብ በር” እየተባለ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በእርሱ ላይም በተደረገው ነገር ይገረሙና ይደነቁ ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መልካምም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 3:10
12 Cross References  

ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሊገ​ለ​ጥ​በት ነው እንጂ እርሱ አል​በ​ደ​ለም፤ ወላ​ጆ​ቹም አል​በ​ደ​ሉም።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል።


እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።


ሁሉም ተገ​ረሙ፤ የሚ​ሉ​ት​ንም አጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እንጃ! ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባ​ባሉ።


ተገ​ረሙ፤ አደ​ነ​ቁም፥ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚህ የሚ​ና​ገ​ሩት ሁሉ የገ​ሊላ ሰዎች አይ​ደ​ሉ​ምን?


ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።”


የዚያ ቦታ ሰዎችም ባወቁት ጊዜ በዙርያው ወዳለ አገር ሁሉ ላኩ፤ ሕመምተኞችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤


ጎረ​ቤ​ቶ​ቹና ቀድሞ የሚ​ያ​ው​ቁት፥ ሲለ​ም​ንም ያዩት የነ​በ​ሩት ግን፥ “ይህ በመ​ን​ገድ ተቀ​ምጦ ይለ​ምን የነ​በ​ረው አይ​ደ​ለም?” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements