Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከዚ​ህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚ​ባ​ለው ተራራ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሰ​ን​በት መን​ገድ ያህል የራቀ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ይህም ተራራ ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል ይርቅ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያን ጊዜ ደብረዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ የደብረ ዘይት ተራራ ከኢየሩሳሌም የሚርቀው የሰንበት መንገድ (አንድ ኪሎ ሜትር) ያኽል ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 1:12
10 Cross References  

እነ​ር​ሱም ሰገ​ዱ​ለ​ትና በታ​ላቅ ደስታ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፤


እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።


ቢታ​ን​ያም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ አም​ስት ምዕ​ራፍ ያህል ቅርብ ነበ​ረች።


ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር።


መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።


እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።


በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፣ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፣ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል።


ደብረ ዘይት ወደ​ሚ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ወዳ​ሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታ​ንያ በቀ​ረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ላከ።


ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements