Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




3 ዮሐንስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወዳጅ ሆይ! ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወዳጅ ሆይ፤ ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለች ሁሉ መልካም ጤንነት እንዲኖርህና በነገር ሁሉ እንዲሳካልህ እጸልያለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወዳጄ ሆይ! በመንፈስ እንዳደግህ ሁሉ፥ በነገር ሁሉ እንዲሳካልህና በመልካም ጤንነት እንድትኖር እጸልያለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ወዳጄ ሆይ! ኑሮህ ሁሉ እንዲሳካልህ፥ ጤንነት እንዲኖርህና እንዲሁም የመንፈስ እርካታ እንድታገኝ እመኝልሃለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።

See the chapter Copy




3 ዮሐንስ 1:2
19 Cross References  

ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኀጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤


ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም እንጂ ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ብቻ አታ​ስቡ።


“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።


ከሁሉም በፊት ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፤ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማረው፤ በኀ​ዘን ላይ ኀዘን እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ብኝ ለእ​ኔም እንጂ ለእሱ ብቻ አይ​ደ​ለም።


እኛ ግን በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፤ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤


ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤


ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements