Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ጢሞቴዎስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከእኔ ጋራ ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎቴ ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋራ ይዘኸው ና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስን ከአንተ ጋር ይዘኸው ና፥ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ። ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።

See the chapter Copy




2 ጢሞቴዎስ 4:11
15 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።


አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።


በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።


በእስያ ያሉቱ ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም ፊሎጎስና ሄርዋጌኔስ ናቸው።


ወዳ​ጃ​ችን ባለ መድ​ኃ​ኒቱ ሉቃ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ ዴማ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል።


ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥


ስለ​ዚ​ህም ተኰ​ራ​ር​ፈው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ፤ በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆ​ስን ይዞ በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄደ።


ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን፥ ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


ራእ​ዩ​ንም ባየ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ልን​ሄድ ወደ​ድን፤ ወን​ጌ​ልን እን​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ራን መስ​ሎ​ና​ልና።


ኋለ​ኞች ፊተ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ ፊተ​ኞ​ችም ኋለ​ኞች ይሆ​ናሉ።”


እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።’ ”


ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።


አሦር አያ​ድ​ነ​ንም፤ በፈ​ረ​ስም ላይ አን​ቀ​መ​ጥም፤ ድሃ​አ​ደ​ጉም በአ​ንተ ዘንድ ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛ​ልና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የእ​ጆ​ቻ​ች​ንን ሥራ አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ አን​ላ​ቸ​ውም።”


በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ።


እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements