Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ሲባም ለንጉሡ፣ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ንጉሡም “እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ቸርነት የማሳየው ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ሲል ጺባን ጠየቀው። ጺባም “ከዮናታን ወንዶች ልጆች አንዱ አሁንም በሕይወት አለ፤ እርሱም እግረ ሽባ ነው” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ንጉሡም፦ የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 9:3
11 Cross References  

ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።


ሰማ​ያዊ አባ​ታ​ችሁ የሚ​ራራ እንደ ሆነ እና​ን​ተም የም​ት​ራሩ ሁኑ።


ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን መረ​ጣ​ቸው፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እና​ን​ተን ዘራ​ቸ​ውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መረጠ።


ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገ​ል​ጋዬ አታ​ለ​ለኝ፥ እኔ ባሪ​ያህ አን​ካሳ ነኝና፦ ከን​ጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህ​ያ​ዬን ጫን​ልኝ፤ እኔም እቀ​መ​ጥ​በ​ታ​ለሁ አል​ሁት።


አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤


ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።


ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሥ ገበታ ሁል​ጊዜ እየ​በላ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ኖረ፤ ሁለት እግ​ሮ​ቹም ሽባ ነበሩ።


እር​ሱም በእኔ በባ​ሪ​ያህ ላይ ክፉ አደ​ረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነህ፤ በፊ​ት​ህም ደስ ያሰ​ኘ​ህን አድ​ርግ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements